ኤጀንሲው ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ

108

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከወረዳ ጀምሮ ባለው መዋቅር ከዛሬ  ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ  መሆኑን ይፋ አደረገ።

ኤጀንሲው በ16 ሞዴል ወረዳዎች ስራ የማስጀመሪያ መርሃግብር እያካሄደ  ይገኛል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ  ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታረቀኝ ገመቹ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በመገኘት መረሃ ግብሩን አስጀምረዋል።

በዚህ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ  ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን እንዳሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ፍጥነትና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እየተሰራባቸው ካሉ ተቋማት መካከል የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አንዱ ነው። 

ኤጀንሲው እያደረገ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እና አገልግሎቱን ለማዘመን ይረዳዋል ነው ያሉት ።  

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም