የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውሉ 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ

342

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በስሩ ለሚገኙና ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ  አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውሉ 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሽከርካሪዎቹን ቁልፍ ለተቋማቱ አስረክበዋል።

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማዘመን ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ተሽከርካሪዎቹ የከተማዋን ገጽታ የሚመጥኑና አገልግሎት አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በከተማዋ ለሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞችና በስራቸው ላሉ ወረዳዎች እንደሚውሉም ጠቁመዋል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም