ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና  ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተገኝተዋል።


 

በአውደ ርዕዩ በመጀመሪያ ደረጃ በምርት ሙከራና ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ስታርት አፖች በመሳተፍ ላይ ናቸው። 

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም የተከፈተው ስታርት አፕ አውደርዕይ እስከ ሚያዚያ 20 ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም