ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በወልቂጤ ከተማ እየተወያዩ ነው

70

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በወልቂጤ ከተማ እየተወያዩ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላም እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሔዱ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም