የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለስምንት አዳዲስ የአመራር አባላት ሹመቶችን ሰጠ

79

ጋምቤላ፤ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ከአመራር የማስፈፀም አቅም ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ከምንጩ ለመፍታት የአመራር ሽግሽግ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ዛሬ አዳዲስ ሹመቶችን የሰጠው በህዝቡ ለሚነሱ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በማሰብ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት፦

1 አቶ ባጓል ጆክ_ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

2. አቶ ቻም ኡቦንግ_ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ቱት ጆክ_ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

4. ዶክተር ቾል ኬድ_ የክልሉ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

5. አቶ ቾል ማቢየል_ የክልሉ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት ኃላፊ

6. አቶ ጉባይ ጆክ_ የክልሉ ጤናና ጤና ነክ ክትትልና ቁጥጥር አገልግሎት ኃላፊ

7. አቶ ላም ታንግ _ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ ጋትዊች ቢየል_ የክልሉ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሹመዋል።

ሹመት የተሰጣቸው የአመራር አባላት በትምህርት ዝግጅታቸው የበቁ፣ በእኩልነት አመለካከት የሚያምኑ፣ በስራ ልምዳቸውና በአፈፃፀማቸው ውጤታማ የሆኑ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የመንግስት ተልዕኮ በአግባቡ ተቀብለው የሚፈፅሙና የሚያስፈፅሙ መሆናቸው ታምኖበታል ሲሉም ተናግረዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም