ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

131

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላን ህልፈተ-ሕይወት በማስመልከት የኃዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሃዘን መግለጫቸው ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለሀገራቸውና ለቀጣናው ሠላምና ደህንነት መረጋገጥ የነበራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አስታውቀዋል።

እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችን ባጋጠመቸው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸው በማለፉ በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

ጀኔራል ፍራነኪስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለኬኒያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ሥራ ሁልጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከኬኒያ ወንድም ህዝቦች ጋር መሆኑን አስረድተዋል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መኮንኖች ቤተሰቦችና ወዳጆች በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም