የኤሌክትሪከ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው 98 በመቶ ተጠናቀቀ

89

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ከቀበና ድልድይ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ክልል ውስጥ የነበረን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛውር ስራ 98 በመቶ ተጠናቋል፡፡

በዚህ የመስመር የማዛወር ስራ 3 ነጥብ 75 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር፣ 4 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የዝቀተኛ መስመር፣16 ትራንስፎርመሮችና 3 ስዊቺንግ ስቴሽኖችን ቀድሞ ከነበሩበት በማንሳት ወደ ተመደበላቸው ቦታ ማዛወር ተችሏል፡፡

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው 103 አዲስ የኮንክሪት ምሰሶዎች፣ 100 አዲስ የእንጨት ምሰሶዎች፣ አንድ ድራም የኤሌክትሪክ ኬብል እና 200 ሜትር የከፍተኛ ቮልቴጅ የመሬት ውስጥ ኬብል ከነባሩ በተጨማሪ ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡


 

ከዚህም በተጨማሪ 98 ነባር የኮንክሪት ምሶሶዎችን የማንሳትና አንድ ስዊቺንግ ስቴሽን በአዲስ ለመቀየር ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ስራው ሲከናወን በአካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ  መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክአገልግሎት  የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም