ዛሬ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል

410

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናይጄሪያዊው አጥቂ ጄሮም ፍሊፕ በ38 ኛው፣ወገኔ ገዛኸኝ በ80ኛው እና አቡበከር ሳኒ በ90ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ኢትዮጵያ መድንን አሸናፊ አድርገውታል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ወሳኝ ሶስት ነጥብ በማግኘት በ22 ነጥብ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአንጻሩ ተጋጣሚው ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌላኛው የ22ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም