ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ የሚከናወኑ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

160

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፡- በሐረር ከተማ ህዝብን ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ባለፈው አንድ ወር በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ለድጋፍና ክትትል ከተመደቡ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ ህዝብን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

በተለይም የአረንጓዴ ልማትና የከተማ ፅዳትና ውበት ስራዎች ሐረርን ለነዋሪዎቿ ምቹና በጎብኚዎች ተመራጭ ከተማ ለማድረግ እንደሚቻል ያመላከተ ነው ብለዋል።

በጽዳትና ውበት፣ በደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ በህገ ወጥ ንግድና ግንባታ እንዲሁም በመንገድ ዳር መብራት ስራዎች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አመራሩ በቅንጅት በመስራቱ ውጤት ማምጣቱን ጠቅሰው በቀጣይም እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በቀጣይም ተቋማት ስራዎቹ ዘላቂ እንዲሆኑ ለማድረግ መረባረብ ይገባቸዋል።

በተለይም የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም