ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢንደስትሪዎችን ጎበኙ

243

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2016 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሀገር በቀል የተሽከርካሪዎች ምርት፣ በኃይል እና ቴሌኮም መለዋወጫ ምርት ዘርፍ ከፍ ያለ ኃይል ተሸካሚ የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት ብሎም በጨርቃጨርቅ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንደስትሪዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም  የሥራ እና ክህሎት፣ መከላከያ፣ ማዕድን፣ ኢንደስትሪ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትሮች መሳተፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። 

ኢንደስትሪዎቹ በሀገር በቀል የተሽከርካሪዎች ምርት፣ በኃይል እና ቴሌኮም መለዋወጫ ምርት ዘርፍ እንደ ከፍ ያለ ኃይል ተሸካሚ የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት ብሎም በጨርቃጨርቅ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ታምርት ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በማደግ ላይ ያለ ተግባራዊ እውነት መሆኑን በመረጃው ተመላክቷል።

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የኢኮኖሚያችን የማዕዘን ድንጋይ እንደመሆኑ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርታማ በሆኑት የሀገር በቀል አምራቾች ስራ ላይ የትኩረት ብርሃን እንደፈነጠቀባቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም