ሀገር በቀል ኩባንያዎች ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ እና የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት በሀይል አቅርቦትና ቴሌኮም ኢንደስትሪ መሳተፋቸው አበረታች ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

156

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፦ ሀገር በቀል ኩባንያዎች ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ እና የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት በሀይል አቅርቦት እና ቴሌኮም ኢንደስትሪ መሳተፋቸው እጅግ አበረታች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኤሌክትሪክ የማከፋፈል ስራ ዐቢይ አካል እንደመሆኑ ዘርፉ ሙሉ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም