የብረት ምርትን ማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲያችን አካል ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

117

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2016 (ኢዜአ)፦ የብረት ምርትን ማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲያችን አካል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎችን ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች በሀገር ውስጥ ማቅረብን እየሠራንበት እንገኛለን ብለዋል።


 

በተጨማሪም የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከትም በእጅጉ ያበረታታል ብለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም