የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው

150

አርባ ምንጭ፤ ሚያዝያ 10/2016(ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ታውቋል።

ንቅናቄው በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን በማህበረሰብ ተሳትፎ ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በአርባ ምንጭ ከተማ ንቅናቄውን ለማስጀመር በተዘጋጀ መድረክ ላይ በፕላስቲክ ብክለት፣ በደን ጭፍጨፋ እና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ወራሳ፣ የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛተ ግጄን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም