የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

336

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2016(ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት 1445ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል እና ዘንድሮ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በሙሉ ይቅርታ ወንድ 637፤ ሴት 11፤ በልዩ ሁኔታ ወንድ 3 ሴት 3 በጠቅላላው 654 ታራሚዎች ሲሆኑ ለ4 ወንዶች ታራሚዎች ደግሞ የእስራት ቅናሽ ተደርጎላቸዋል።

በክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ስር ባሉ ሰባት ማረሚያ ተቋማት ከሚገኙ የህግ ታራሚዎች መካከል በ2016 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር 658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም