ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሸዋል ዒድ በዓል አብሮነትን በሚያጎላ መልኩ እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

150

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2016(ኢዜአ)፡- የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሸዋል ዒድ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አብሮነትንና ፍቅርን በሚያጎላ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በክልሉ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የሸዋል ዒድ በዓል ከመቼውም ጊዜ በላይ በታላቅ ድምቀት እና ስኬት መጠናቀቁን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ለበዓሉ ስኬት ሚና የነበራቸውን የክልሉ ህዝብ፣ የፀጥታ እና ህግ አስከባሪ አካላት፣ የአጎራባች ክልሎች ልዑካን እንዲሁም ሌሎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርዕስ መስተዳድሩ መግለጻቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም