ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ጋር ተወያዩ

647

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር  ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ በመዲናችን እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡


 

አዲስ አበባ ከአሜሪካ ከተሞች ጋር ያላትን የእህትማማችነት ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያም መወያየታቸውንም ከንቲባዋ አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም