በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ "አስተውሎት" የተሰኘ ሳይንሳዊ ፊልም ተመረቀ

283

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ "አስተውሎት" የተሰኘ ሳይንሳዊ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፣ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሻለ ነገ ማየት የሚያስችል ወሳኝ ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልጸዋል።


 

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የማሰብ፣ የመገንዘብና ምክንታዊ የመሆን አቅምን በማዳበር በሰውኛ ጥበብ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተጀምሮ አሁን ባለበት ደረጃ ላይ እንዲገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።


 

ኢንስቲትዩቱ አሁን ላይ ለሀገር የሚበጁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከሰውኛ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው "አስተውሎት" የተሰኘውና በዕውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ሳይንሳዊ ፊልም ለአንድ አመት ዝግጅት የተደረገበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም