አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ

242

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ዋና ጸሃፊ ሼክ መንሱር ቢን ሙስሰላም ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በድርጅቱ መካከል ትብብርን የበለጠ ማሳደግ በሚቻልበት  ዙሪያ የተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው ድርጅቱ እውቀትን በማፍለቅ እና አካታች የትምህርት ስርዓት እንዲገነባ በአለምአቀፍ ደረጃ እየሰራ እንደሚገኝም ተነስቷል።

ድርጅቱ በደቡብ ደቡብ ማዕቀፍ በአባል አገሮቹ መካከል የትምህርት፣ የቴክኒክ እና የገንዘብ ትብብር ለመፍጠር እያገለገለ እንደሆነ መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም