ጀርመን ለስምንት ሆስፒታሎች የ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

77

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የጀርመን መንግስት በጀርመን ልማት ባንክ አማካይነት ለስምንት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የህክምና ቁሳቁሶቹም የትምህርትና የጤና ሚኒስቴር አመራሮች፣ የጀርመን ልማት ባንክ ተወካይ፣ የጀርመን ኤምባሲና የሆስፒታሎቹ ሃላፊዎች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላዝይድ ሆስፒታል፣ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አዳማ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል፣ ጂማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ማዕከል፣ አይደር ሪፈራል ሆስፒታልና አርባምንጭ ሪፈራል ሆስፒታሎች ናቸው።

ለሆስፒታሎቹ ከሕክምና ቁሳቁስ በተጨማሪ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

ጀርመን ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ እያደረገች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም