በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በባህልና በታሪክ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በባህልና በታሪክ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው
ጂንካ ፤ ሚያዝያ 7/2016 (ኢዜአ)፡- በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በባህልና በታሪክ ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።
አውደ ጥናቱ "የኢትዮጵያ አመሰራረት እና የሀገር በቀል አውቀት ለግጭት አፈታት" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል።
በመድረኩ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤል ዶነሃም ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የባህል ተመራማሪዎች ጋር በመተባበር በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ያካሄዱትን ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በእዚህም በኢትዮጵያ አመሰራረት፣ በሀገር በቀል ዕውቀቶች እና በግጭት አፈታት ዘዴዎች ላይ በማተኮር ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ ከሀዋሳ፣ ከአርባ ምንጭና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ የጥናት አቅራቢዎች ተገኝተዋል።
እንዲሁም ከአሪ ዞን እና ከደቡብ ኦሞ ዞን የተጋበዙ የዘርፉ ምሁራንና የማህበረሰብ ተወካዮችም በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
በዩኒቨርሲቲው መካሄድ የጀመረው አውደ ጥናቱ ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል።