ቀጥታ፡

የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016 (ኢዜአ)፦ የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የተሽከርካሪ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስረክበዋል።


 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፥ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እና የተሳካ እንዲሆን ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።


 

ከጃፓን መንግስት በድጋፍ የተገኙ ተሽከርካሪዎች፥ ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚያከናውናቸውን የመስክ ስራዎች ለማቀላጠፍ ያግዛሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ መሰረታዊ በሚባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኗን ጠቅሰዋል።


 

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው እንደገለጹት ጃፓን ለኮሚሽኑ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም