ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ተጀመረ

236

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፦ ሁለተኛው ዓለም  አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ  መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ ፣ ሰብዓዊ  ክብርን መጠበቅ፣ አካባቢን መጠበቅ፣  የጥላቻ ንግግርንና መጤ  ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ  የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።

ጉባዔው  የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት  ጉባዔ  ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በኢፌዲሪ  ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ እና ነገ የሚካሔድ ይሆናል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም