ቀጥታ፡

የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድልና ተግዳሮቶች ላይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 7/2016 (ኢዜአ)፦ የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድልና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ  በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

የምክክር መድረኩ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ትብብር  መዘጋጀቱ ተገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልልና የፌደራል የስራ ኃላፊዎች፣ የማሽነሪ አምራችና አቅራቢ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል። 

በመድረኩ የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዕድሎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም ቀጣይ ስራዎችን የሚያመላክቱ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም