ኢትዮጵያ በብሪክስ የሚኖራትን ተጠቃሚነት በሚያሳድግ እና ለማዕቀፉ መጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

1016

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት የሚኖራትን ተጠቃሚነት ክፍ ለማድረግና ለማዕቀፉ መጠናከር ጉልህ አስተዋጽዖ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።

በብሪክስ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ ሦስተኛ ስብሰባ ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተካሂዷል።

ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አገራችን በዘላቂነት የምትከተለው ስትራቴጂ እና የአገራችን ተቋማት በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ እያደረጉ ያሉትን ተሳትፎ ዳስሷል፡፡ 


 

ኮሚቴው በተጨማሪም አገራችን በማዕቀፉ አባልነት የምታደርገውን ሽግግር ለማሳካት፣ ተጠቃሚነቷን ከፍ ለማድረግ፣ብሎም ለማዕቀፉ መጠናከር ጉልህ አስተዋጽዖ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል የሆነችው የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተጨማሪ ዕድሎችን ለመጠቀም ነው።

በተጨማሪም የዓለምን የባለብዙ ወገን ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከር የበኩሏን አስተዋጽዖ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም