ኮሩ ባደረገው ተከታታይ ዘመቻ የአሸባሪው የሸኔ ቡድን አባላት ለመከላከያ እጅ እየሠጡ ነው

680

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 05/2016 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ኮሩ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ እየተደመሰሰ እና እጅ እየሠጠ መሆኑ ተገልጿል።

የሽብር ቡድኑን በመቀላቀል ለሽብር ቡድኑ በሎጀስቲክስ ፣ በተተኳሽ አቅርቦት፣ በሶሻል ሚዲያዎች የአሸባሪው ክንፍ በመሆን የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የሸኔ አባላት የነበሩበት ሁኔታ የተሳሳተ እንደነበርም ገልፀዋል።


 

የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦኘሬሽናል ኮሎኔል ብርሃኑ አዱኛ እንዳሉት ኮሩ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ባደረገው ዘመቻ አብዛኛው የሽብር ቡድኑ ሃይል ሲደመሰሰ ቀሪው በሰላማዊ መንገድ እጁን ለመሥጠት መገደዱን ተናግረዋል።

ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር 1 ብሬን፣ 1 ስናይፐር ፣ 50 ክላሽ፣ 29 ቦንብ ፣ 2892 የክላሽ ጥይት፣ 72 የክላሽ ካዝና፣ 350 የብሬን ጥይት ገቢ መደረጉን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ የሽብር በበኩላቸው ቡድኑ በዞኑ ቦሰት ወረዳ፣ ሊበን ወረዳ፣ቦራ ወረዳ እና ፈንታሌ ወረዳዎችን በመያዝ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ በማድረግ በመሰረተ ልማቶች ላይ አደጋ ሲፈጥሩ እንደቆዩም ተናግረዋል።

የሸኔ ቡድን ተደጋጋሚ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ባለመቀበል በደል ሲፈፅሙ የቆየ ቢሆንም መከላከያና የክልሉ የፀጥታ ሃይል በወሰደው እርምጃ እጃቸውን መሥጠታቸውንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም