ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2016(ኢዜአ)፦ ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ።
ማሽነሪዎቹ በሐረር መርከብ ተጭነው ጅቡቲ ወደብ መራገፋቸውንና አሁን ላይም በከባድ የየብስ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ መሆኑን ገልጿል።
ለሚ የሲሚንቶ ፋብሪካ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ የሚገኝ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ነው።