ከሀይል ቋት የራቁ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተፈረመ - ኢዜአ አማርኛ
ከሀይል ቋት የራቁ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ሶልዩሽን ካምፖኒ ጋር ከዋናው የሀይል ቋት የራቁ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ሶልዩሽን ካምፖኒ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለው መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ሶልዩሽን ካምፖኒ የኢትዮጵያ ቢሮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚሻይል ሊዩ ናቸው።
ከዋናው የሀይል ቋት የራቁ አካባቢዎችን በኦፍ ግሪድ አማራጭ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ፣ በኤሌክትሪክ ሀይል ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ቻርጅ ሲስተም እና የተቋሙን አሰራር በሚያዘምኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ በጋራ ለመሰራት ያለመ ስምምነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም አገልግሎትን ለማቀላጠፍ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።