ቀጥታ፡

አየር ኃይል ያሰለጠናቸውን ቪዥን 2035 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰልጣኞች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ቪዥን 2035 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰልጣኞችን በደማቅ ስነ-ስርዓት እያስመረቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በያዘው ዕቅድ መሠረት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቪዥን 2035 የተሰኙ የመጀመሪያ ዙር የአየር መንገድ የበረራ ሠልጣኞችን በሥነ-ልቦናና በአካል ብቃት አሰልጥኖ እያስመረቀ ይገኛል።


 

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ መሥፍን ጣሳው እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም