አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከሻንግዱ ከተማ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከሻንግዱ ከተማ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 04/2016 (ኢዜአ):- በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው በቻይና የሻንግዱ ከተማ መዘጋጃ ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኃላፊ ጂያንግ ቢን(ዶ/ር) ጋር በዘርፈ ብዙ ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መምከራቸው ተገለጸ።
በውይይታቸውም በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መምከራቸው ታውቋል።
በዚህም ሁለቱ ወገኖች በከተሞች ልማት፣ በጤና ፣ በትምህርትና ግብርና መስኮች በጋራ መስራት ስለሚችሉበት ሁኔታ መምከራቸው ተገልጿል።