ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ

583

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አጥቂው አሊ ሱሌይማን በ39ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሃዋሳ ከተማ መሪ መሆን ችሎ ነበር።

ከእረፍት መልስ ዩጋንዳዊው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች ሳይመን ፒተር በ50ኛው እና ኪቲካ ጀማ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸናፊ አድርገውታል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥቡን ወደ 43 ከፍ በማድረግ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

በአንጻሩ ሃዋሳ ከተማ በ26 ነጥብ በነበረበት 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሃዋሳ ከተማው አጥቂና የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ አሊ ሱሌይማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛት ወደ 12 ከፍ አድርጓል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም