የ'ስታርት አፕ' ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ በዘርፉ ያሉ ተሳታፊዎችን የፈጠራ ምናብ ስፋት ብሎም ችሎታ ማሳያዎች ቀርበውበታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3/2016(ኢዜአ)፦ በሳይንስ ሙዚየም እየታየ ያለው የ'ስታርት አፕ' ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ በዘርፉ ያሉ ተሳታፊዎችን ተምኔት፣ የፈጠራ ምናብ ስፋት ብሎም ችሎታ ማሳያዎች ቀርበውበታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳይንስ ሙዚየም እየታየ ያለውን የ'ስታርት አፕ' ኢትዮጵያ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሁላችሁም አውደ ርዕዩን በመመልከት ከተሳታፊዎቹ ጋር እንድትወያዩ እጋብዛለሁ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም