ቀጥታ፡

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የ1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም መጠናቀቁን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2/2016(ኢዜአ)፦ በመላው ሀገሪቱ የተከበረው 1445ኛው ዓመተ ሂጅራ ኢድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገልጿል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ህዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራውን በብቃት መወጣቱ ተጠቅሷል።

በጥበቃው ላይ የተሰማሩት የፀጥታ አካላት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከራሳቸው በፊት ህዝቡን በማስቀደም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ ማሳካቱን ገልጿል።

ለዚህም የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

መላው የሀገራችን ህዝብም ከግብረ-ኃይሉ የተሰጠውን መግለጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላደረገው ቀና ትብብርና ድጋፍም የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አመስግኗል።

በመጨረሻም ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡት የእስልምና እምነት ተከታዮችና የሀይማኖት አባቶች፣ በዓሉን ላስተባበሩና ለመሩት ወጣቶች ላደረጉት ከፍተኛ ትብብር የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ምስጋና ማቅረቡን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም