1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 2/2016 (ኢዜአ)፦ 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ በአዲስ አበባ ስታድየም እየተከበረ ሲሆን የእምነቱ ተከታዮችም በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ እያመሩ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እለቱ ሲከበር በመተዛዘን፣ በመደጋገፍ እና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡