የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2016(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በሶስት ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቅሷል።
በዚህም በዘርፉ ብቃት ያላቸው አመራሮች ማፍራት፣ በዘርፉ አንቱታን ላተረፉ አመራሮች ዕውቅና መስጠት እና የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ማዘጋጀት እንደሆነ ተጠቅሷል።