ቀጥታ፡

ወደብ ከደረሰው ከ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 92 በመቶው ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2016(ኢዜአ)፦ ለ2016/17 የምርት ዘመን ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው ከ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 92 በመቶው ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለጸ።

ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ጅቡቲ ወደብ ከደረሰ 11 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ማዳበሪያ ውስጥ 92 በመቶው ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።

በዚህም ለ2016/17 የምርት ዘመን ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው 11 ሚሊየን 160 ሺህ 474 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን 10 ሚሊየን 270 ሺህ 266 ኩንታል (92 በመቶ) ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል። 

በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም 500 ሺህ 480 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ወደብ የደረሰች ሲሆን፣ ከ18 ቀናት በኋላ 636 ሺህ 600 ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም