ቀጥታ፡

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016 (ኢዜአ)፦ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ጥሪ አቀረቡ።

አምባሳደር ደመቀ ጥሪውን ያቀረቡት በህንድ ሞምባይ ከተማ የኤስያ አፍሪካ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው ስድሥተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ አመራሮች ፎረም ሲካሄድ ነው።


 

አምባሳደሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማዕድን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና ቱሪዝም ዘርፎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች መሆናቸውን በፎረሙ ላይ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ኩባንያዎች መካከል የህንድ ባለሀብቶች በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ጨምረው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም