ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም ተከፈተ  

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል። 

ኤግዚቢሽኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከፍተውታል። 

በኤግዚቢሽኑ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ በመጀመሪያ ደረጃ የሚገኙ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩና ወደ ገበያ ደረጃ የተቀላቀሉ ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።  


 

ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20/2016 ዓ.ም በሚካሄደው በዚሁ ኤግዚቢሽን 500 የሚጠጉ ስታርት አፖች ምርቶቻቸውን እንደሚያስተዋውቁም ተገልጿል። 

ባሳለፍነው ሳምንት ስታርት አፕ በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ፣ የሚገጥሙ ፈተናዎችና መውጫ መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በሳይንስ ሙዚየም መካሄዱ ይታወሳል።
 

 
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም