ቀጥታ፡

ለክልሉ ሰላም መጠናከር በህብረት እንደሚቆሙ የሀርቡ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦ ለአማራ ክልል ሰላም መጠናከር በህብረት በመቆም ለሀገሪቱ ብልጽግና እውን መሆን እንደሚተጉ በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በከተማዋ ለውጡን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለክልላችን ሰላም በህብረት እንቆማለን፣ ለሀገራችን ብልፅግና እውን መሆን እንተጋለን፤ በጋራ ጥረታችን ሰላማችንን እናረጋግጣለን የሚሉ መልእክቶችን የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎቹ በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ።


 

በተጨማሪም በጥቂት ፅንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገርና ህዝብ የለንም፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬያችን መገለጫ ነው፣ ውስጣዊ ሠላማችንን በማፅናት ውጫዊ ተፅዕኖዎችን በድል እንወጣለን፣ የክልላችንን አንፃራዊ ሠላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሠላም እናሸጋግረዋለን የሚሉ መልእክቶችም ተንጸባርቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም