በሰቆጣ ከተማ የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸውን ውጤቶች የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016 (ኢዜአ)፦ ባለፉት 6 ዓመታት ለውጡን ተከትሎ ለተገኙ ስኬቶች እውቅና የሚሰጥ ህዝባዊ ሰልፍ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።


 

በድጋፍ ሰልፉ "እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሃገራችን ሰላምና ብልፅግና የበኩላችንን ሚና እንወጣለን፤ሰላማችን በእያንዳድንዳችን ቤት ናት፤የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድልና ስኬት የአባቶቻችንን ገድል የደገምንበት ታሪካዊ አሻራ ነው፤የላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጽያ ብልፅግና" የሚሉ መልዕክቶች ተንፀባቀዋል።

ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር በተጨማሪም በብሄረሰብ አስተዳደሩ በሚገኙ ወረዳዎች ላይም ሃገራዊ ለውጡንና መንግስቱን የሚደግፍ የሃገር ሽማግሌዎች ፣የመንግስት ሰራተኞች፣ሴቶችና ወጣቶች የተሳተፉበት ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም