ቀጥታ፡

በአምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ሳዑዲ አረቢያ ገባ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2016(ኢዜአ)፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራና የተለያዩ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ሳዑዲ አረቢያ ገብቷል፡፡

ልዑኩ በህገወጥ መንገድ ድንበር ተሻግረው በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንዲቻል በጉዳዩ ላይ ለመምከር ሳውዲ አረቢያ ገብቷል፡፡

ልዑኩ በሪያድ በመገኘት ከሳዑዲ አረቢያ አቻው ጋር በሳዑዲ ውስጥ የሚገኙ ህገ-ወጥ ፍልሰተኛ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በወቅቱ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አሊ አል-ዩሱፍ ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ 

ሁለቱ ሀገራት የመንግስታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ላይ እንደሚገኙ ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ፍልሰትን ለመከላከል እየሰራች መሆኑንም አምባሳደር ብርቱካን  በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል። 

የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር በበኩላቸው ከልዑካን ቡድኑ ጋር ያደረጉት ውይይት ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትም ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን አመልክተው፣ በሀገራቸው በኩል ህገ-ወጥ ፍልሰተኞች በማቆያ ቦታዎች ሳይጉላሉ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲፈጠር ይሰራል ብለዋል። 

የሀገራቸው መንግስትም በህጋዊ መንገድ ለሥራ የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን እንደሚያበረታታ ጠቅሰው፣ የሀገራቱን ንግድና ኢንቨስትመንትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰራም ገልጸዋል።
 
ውይይቱን ተከትሎ በህገ ወጥ መንገድ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ፍልሰተኛ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ተግባር በቅርቡ እንደሚጀመርም በመረጃው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም