በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2016 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለሀድያ ሆሳዕና ዳዋ ሁጤሳ እና ብሩክ ማርቆስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያላዳነውን ብቸኛ ጎል ዮሴፍ ታረቀኝ ማስቆጠሩን ሊግ ካምፓኒው አስታውቋል።
ከደቂቃዎች በኋላ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።