የኢድ በአል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡእ ይከበራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢድ በአል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡእ ይከበራል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/2016(ኢዜአ)፦ የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በአል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡእ እንደሚሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፤ 1 ሺህ 445ኛውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በአል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡእ ይከበራል ብለዋል።
የኢድ በአል የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት ማሳያ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ እለቱን ስናከብር በመተዛዘን፣ በመደጋገፍና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በረመዳን ወር የታየው መረዳዳትና መልካም ስነ ምግባር ከረመዳን በኋላም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
የኢድ አል ፈጥር በአል የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት እንዲሆን በመመኘት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ከወዲሁ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።