“ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
“ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል

ሀዋሳ ፤ መጋቢት 28/2016(ኢዜአ)፦ ሲዳማ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በሀዋሳ ከተማ የፍቅር ሀይቅ ዳርቻ በሚገኘው 'ሶሬሳ ጉዱማሌ' እየተከበረ ነው።
''ፊቼ ጨምበላላ'' በዓል አብሮነት፣ ሰላም፣ መረዳዳትን በሚያጠናክሩ ክንውኖች ታጅቦ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በሲዳማ ባህላዊ ጭፈራ በሆነው 'ቄጣላ' ጨዋታና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በዓሉ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ታድመዋል።
የሲዳማ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ወሰንየለህ ሰምኦን፣ በዓሉ ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ ብስራት ነው ብለዋል።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል።