በዲላና ጂንካ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
በዲላና ጂንካ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል
ዲላ/ጂንካ ፤ መጋቢት 27/2016(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላና ጂንካ ከተሞች "ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን፤ ለውጡን እናፀናለን" በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በክልሉ በጌዴኦ ዞን ዲላና በአሪ ዞን ጂንካ እየተካሄዱ በሚገኙት የድጋፍ ሰልፎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ከለውጡ ወዲህ ባለፉት ስድስት ዓመታት በአገሪቱ የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚደግፉ ሰልፈኞቹ እየገለጹ ነው።
"በጋራ ጥረት ሰላማችንን እናረጋግጣለን ፣ አንድነታችንን በማፅናት የኢትዮጵያን ብልፅግና እናፋጥናለን፣ አገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር በሚደረገው እንቅንቃሴ ሁሉ በፅናት እንቆማለን፣ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ እንደጀመርነው እናጠናቅቀዋለን፣ ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን የሚሉ መልዕክቶች ሰልፈኞቹ እያስተላለፉ ይገኛሉ።