ቀጥታ፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከብራዚል አቻቸው ጋር በግብርናው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2016 (ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከብራዚል አቻቸው ጋር በግብርናው ዘርፍ ላይ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በብራዚል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በግብርናው ዘርፍ በሁሉም መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት እንደሚቻል የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች መግባባታቸው ተገልጿል፡፡

ይህም የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያጠናክር ከመሆኑም ባሻገር በብራዚል መንግስት በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ መልካም ተሞክሮዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ምቹ መደላድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

ሁለቱም ሚኒስትሮች በዘርፉ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገው መግባባት ላይ መድረሳቸውም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም