ጃፓን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች - ኢዜአ አማርኛ
ጃፓን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2016(ኢዜአ)፦ ጃፓን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች አምባሳደሩን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱም በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሁናዊ ተግባራት በተመለከተ በዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጻ እና ማብራርያ ተደርጎላቸዋል፡፡
አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ለተደረገላቸው ገለፃ እና ማብራሪያ ምስጋና አቅርበው በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የምክክር ሂደት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ባለሙሉ ተስፋ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
ሀገራቸው ጃፓን ለሂደቱ መሳካት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን ከምክክር ኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።