ቀጥታ፡

የዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ብድር ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2016(ኢዜአ)፦ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልና የዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ብድር ተጠቃሚ የሆኑ የኢንተርፕራይዞች የስራ እንቅስቃሴን  ጎበኙ።

የስራ ኃላፊዎቹም በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት በአዲስ አበባ ሃያት እና ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙትን የኢቲኤም የጨርቃጨርቅና አሁን የፕላስቲክ ማቀነባበሪያ ኢንተርፕራይዞችን ነው ተዘዋውረው የጎበኙት። 

በጉብኝቱም የኢንዳስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ በዓለም ባንክ የስነ-ምግባር እና የውስጥ ፍትሕ አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ሊሳ ሮዘን፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር)፣ ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። 

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ያደረገውን የፕሮጀክት ድጋፍ አፈፃጸም ምልከታ ማድረግ የስራ ጉብኝቱ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም