ቀጥታ፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የተጀመረበት 13ኛ ዓመት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፤መጋቢት 24/2016 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 13ኛ ዓመት በዓል 'በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉ እየተከበረ ያለው በስዕልና ፎቶ አውደ ርዕይ እንዲሁም በፓናል ውይይት ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የግድቡን የ13 ዓመት የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የቀረበውን የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም