በአዲስ አበባ የሚሰጠው የመሬት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ተሸጋግሯል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2016(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ የሚሰጠው  የመሬት  አገልግሎት  ሙሉ በሙሉ  ወደ ዲጂታል  መሸጋገሩን  የአዲስ  አበባ  መሬት  ልማትና አስተዳደር  ቢሮ አስታወቀ ።

የቢሮው  ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው  ለመገናኛ  ብዙሃን  በሰጡት መግለጫ  ቢሮው ለአገልግሎት  ፈላጊዎች  ዘመናዊ  እና  የተሳለጠ  አገልግሎት  ለመስጠት  የሚያስችሉ  ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። 

በአሁኑ ወቅትም 700 ሺህ ፋይሎች ወደ ዲጂታል  መቀየራቸውን ገልጸው 'ሰርቨር'  ላይ መጫኑንም አስረድተዋል። 

16   አገልግሎቶችን ደግሞ ሙሉ በሙሉ  በኦንላይን መስጠት የተጀመረ በመሆኑ ደንበኞች  ካሉበት ቦታ   አገልግሎት  ማግኘት  እንደሚችሉ አብራርተዋል።  

ከወሳኝ  ኩነት፣  ቴሌ ብርና ሌሎች  መሰል አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመቀናጀት  ለደንበኞች  የተሻለ  አገልግሎት  በመስጠት  እርካታውን ለመጨመር   ተግባራዊ  እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል ።

ቢሮው 'ቴኑዩር ኢንፎርሜሽን  አስተዳደር  ሲስትም አልምቶ'  ስራ ላይ   ማዋሉን ገልጸው፤  አሰራሩ  ለዜጎች  የተደራጀ  አገልግሎት  በመስጠት  ውጤታማ የሚያደርግ  መሆኑን  አብራርተዋል። 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም