በሰርቢያ ቤልግሬድ በተዘጋጀ የወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

253

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2016 (ኢዜአ)፡- በሰርቢያ ቤልግሬድ በተዘጋጀው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል፡፡

በዚህም ማርታ አለማየሁ በ19 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ አንደኛ፣ አሳየች አይቸው በ19 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ ሁለተኛ እንዲሁም ሮቤ ዲዳ በ19 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ ሶስተኛ ሆነው በመግባት የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡

እንዲሁም አትሌት የኔዋ ንብረት በ19 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ 6ኛ፣ ለምለም ንብረት በ20 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ 8ኛ ሽቶ ጉሚ ደግሞ በ20 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ 9ኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዝገበ ስሜ የብር ሜዳልያ ማስመዝገቡም በመረጃው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም